Saturday, May 2, 2026
HomeNews & EventDevelopmentየአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን የሀረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን...

የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን የሀረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው በተቋሙ ያሉ አጠቃላይ የፋይል እንቅስቃሴዎችን በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ ኮምፒተራይዝድ የሆነ አሰራር መዘርጋቱን ገልጿል፡፡ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን ለተገልጋይ ቀልጣፋ እና ምቹ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት ማከናወኑን በሀረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ሸኪብ አብዱራህማን ገልፀዋል፡፡ በዚህም እያንዳንዱ ተገልጋይ የሚፈልገውን ስራንያለ እንግልት ማግኘት የሚችሉበትና አቅጣጫ ጠቋሚዎችን የማዘጋጀት ፣ በአገልግሎቱ ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ዘመናዊ የማቅረቢያ ሲስተም የመዘርጋት ስራዎች እና በርካታ አገልግሎቱን የሚያዘምኑ ተግባራት መከናወኑን አብራርተዋል፡፡ የተቋሙ እያንዳንዱ አገልጋይ ማንነቱን እና የስራ ድርሻውን የሚገልፅ ባጅ እንዲያደርጉ እና በጠረፄዛቸው ላይ እንዲያስቀምጡ መደረጉን፣በመሬት ልማትና ግንባታ ፍቃድ ላይ ያሉ ባለሞያዎች መለያ ልብስ ለብሰው አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ተገልጋዮች ወደ ቢሮ ሲመጡ ሊያሟሉ የሚገባቸውን ነገሮች በቴክኖሎጂ በመታገዝ በስክሪን እንደሚመለከቱ መደረጉንና በተጨማሪም በሚሰጡ አገልግሎቶች ተገልጋዪ ማሟላት ያለበትን በተቋሙ በተዘጋጀ ድህረ ገፅ የሚያገኙበት መንገድ መሟላቱን ጠቁመዋል፡፡ ሌላው ቅሬታ የሚነሳበት ተገልጋይ በመጣበት ቅደም ተከተል አለመስተናገድ ችግርን ለመቅረፍ ቦኖ በማሳተም እና ሁሉም በተራው የሚስተናገድበት አግባብ መፈጠሩን አቶ ሸኪብ ተናግረዋል፡፡ተቋሙ በርካታ ተገልጋይን የሚያስተናግድ በመሆኑ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ቅሬታዎች እንደሚነሳበት ጠቁመው የፋይል መጥፋት ደግሞ ለቅሬታዎች ዋነኛው በመሆኑ ይህን በመገንዘብ ሁሉንም ፋይሎች በቴክሎጂ በመታገዝ ኮምፒተር ላይ በመጫን ኔትወርክ የማድረግ ስራ ተሰርቷልም ይላሉ፡፡ እያንዳንዱ ሰነዶች ፣ ፋይሎች በኮምፒተር ተመዝግበው እንዲቀመጡ መደረጉን የገለፁት በቢሮው የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር አቶ አሚር አቡዱከሪም ሲሆኑ ይህም የመረጃ መጥፋትና በወረቀት የተቀመጡትን ፋይሎች በቀላሉ ለማግኘት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡ እኛም ተዘዋውረን እንደተመለከትነው እና የተቋሙ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪዎች እንዳረጋገጡት የእያንዳንዱ ተገልጋይ በቴክኖሎጂ በመታገዝ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ቅሬታዎችን ለመቀነስ ማስቻሉን ገልፀዋል፡፡

RELATED ARTICLES

Most Popular

Recent Comments