Thursday, April 30, 2026
HomeNews & EventLand holding registration agencyበከተማ ቦታ ኪራይና የከተማ ቤት ግብር አፈጻጸም በተመለከተ ከንግድ ማህበረሰብና ከባለሃብቱ ጋር...

በከተማ ቦታ ኪራይና የከተማ ቤት ግብር አፈጻጸም በተመለከተ ከንግድ ማህበረሰብና ከባለሃብቱ ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ።

የከተማ ቦታ ኪራይና የከተማ ቤት ግብር የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም ውይይት እና የ2018 በጀት አመት እቅድ ዙሪያ በጋራ ለመስራት ከንግድ ማህበረሰብና ባለሃብት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል ።

በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ይዞታ መረጃና ምዝገባ ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም አህመድ በመክፈቻ ንግግራቸው ከመሬት እና ከንብረት ጋር የተያያዙ ግብር መሰብሰብ ለሀገር እና ለአከባቢ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እንደመሆኑ የከተማ ቦታ ኪራይና የከተማ ቤት ግብር የመሰብሰብ ስራን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑና የ2018 ዕቅድን የበለጠ በውጤታማነት ለመፈጸም ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ፤ በገቢዎች ባለስልጣን እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤት ተቋማት መካካል በ2017 በጀት አመት የነበረውን ቅንጂታዊ አሰራር ይበልጥ በማጎልበት መስራት የሚያስፈልግ እንደሆነ ገልፀዋል።

የስልጠናዉን መድረክ አስፈላጊነት የንግድ ማህበረሰብና ባለሃብት የከተማ ቦታ ኪራይና የከተማ ቤት ግብር አሰራርን በመረዳት እና የከተማ ቦታ ኪራይና የከተማ ቤት ግብር ገቢ አሰባሰብ ዙርያ ያጋጠማቸው ችግሮችን በመለየት ለቀጣይ የ2018 በጀት አመት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ መሆኑንም ገልጸዋል ።

የገቢዎች ባለስልጣን ኃላፊ አቶ ያሲን አብዱላህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ የከተማ ቦታ ኪራይና የከተማ ቤት ግብር ለአንድ ሀገር የሚኖረውን የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ከግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት የገቢ አሰባሰብ ስርአት በማሻሻል መንግስት ማግኝነት ያለበትን ግብር በሃላፊነት መሰብሰብ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል ።

በመድረኩም የከተማ ቦታ ኪራይና የከተማ ቤት ግብር የ2017 አፈጻጸም ጥናታዊ ፅሁፍ በአቶ ሻምበል አስፋው ቀርቧል ። በቀረበው ሰነድ ዙሪያም በመድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎች አስተያየት እና ጥያቄዎችን በማንሳት በስፋት የተወያዪ ሲሆን በመጨረሻም የሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ሃላፊ አቶ አዩብ አህመድ ታክስና ግብር በማይከፍል እንዲሁም በደንብ ና አዋጅ የተቀመጠውን ተግባራዊ በማያደርግ በህግ እንደሚያሰጠይቅ በመረዳት ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ የኪራይ ሰብሰቢነትን በጋራ መታገልና መከላከል እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈው ውይይቱን አጠናቀዋል።

RELATED ARTICLES

Most Popular

Recent Comments