Monday, June 15, 2026
HomeNews & EventDevelopmentስድስተኛ ዙር የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

ስድስተኛ ዙር የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

የሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለስልጣን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገዉ አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በሐረሪ ክልል በተለያዩ አካባቢ የሚገኙ (1ኛ-አንደኛ መንገድ አሚር ኑር ፖሊስ ጣቢያ : 2ኛ-ጤና ቢሮ ፊት ለፊት : 3ኛ-ቀላዳንባ እና 4ኛ-ማልቴዝ ጀርባ ) ለንግድ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በመደበኛ የሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።በመሆኑም፡-

• ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሚያዚያ 28/2018 ዓ/ም እለተ እሮብ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽ ቢሮ በቢሮ ቁጥር 34 ዘወትር በስራቀናት እና በስራ ሰአት መግዛት ይችላሉ፡፡

• ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በመግዛት ለቦታዎቹ በካሬ ሜትር የሚያቀርቡትን ዋጋ እና የሚከፍሉትን የሊዝ ቅድመ ክፍያ በጨረታ ማወዳደሪያ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አደርጎ ለጨረታው ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ግንቦት 11 እለተ ማክሰኞ 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰአት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

• ጨረታው በቀን 11/9/2018 ዓ/ም ከቀኑ11፡00 ሰአት ተዘግቶ ፤በቀን 12/9/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አራተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል፡፡

• ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ቦታ የጠቅላላ የቦታው ስፋት በመነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኝው ውጤት 5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

• ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሊዝ ዋጋ 80 በመቶ ነጥብ ሲኖረው የቅድሚያ ክፍያ መጠን ደግሞ 20 በመቶ ነጥብ ይኖረዋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሁለቱ ነጥቦች ድምር በሚገኝ ውጤት ይሆናል።

• ተጫራቾች የሚያቀርቡት የቅድሚያ ክፍያ መጠን ከአጠቃላይ የሊዝ ክፍያ ለንግድ ከ20 በመቶ ማነስ የለበትም፡፡

• የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በግልፅ በይፋ ከተገለፀ በኃላ በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

• ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡

• ቢሮው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ> በስልክ ቁጥር 0919121917 ወይም 0910415925 ዘወትር በስራ ሰአት በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

RELATED ARTICLES

Most Popular

Recent Comments