የመሬት ልማት አስተዳደር ባለስልጣን
የተቋሙ ራዕይ
የሐረሪ ክልል ከተማን በፕላን የምትመራ፤በቂ የለማ መሬት አቅርቦት፤ የንብረት ዋስትና የተረጋገጠበት፤ ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ በመዘርጋት በሐገር አቀፍ ደረጃ ለኑሮ ምቹና ተወዳዳሪ ከተማ ተፈጥሮ ማየት ነዉ፡፡
የተቋሙ ተልዕኮ
ባለድርሻ አካላት እና ባለጉዳዮች ፍላጎት በመለየት የማልማት አቅምን እና የከተማውን ፕላን መሰረት ያደረገ የለማ መሬት አቅርቦት ማረጋገጥ እንዲሁም አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን ግልፅ፤ ፍትሃዊ ፤ አሳታፊ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ በማደረግ የከተማውን ነዋሪ እርካታ እና መልካም አስተዳደር ማረጋገጥ፡፡
የተቋሙ እሴት
-
ግልፅና ተጠያቂነት
-
ለህግ የበላይነት መገዛት
-
ያለ አድሎ ህዝብን ማገልገል
-
አሳታፊነት
-
ታማኝነት እና ታዕማኒነት
-
ህብረተሰብ ተኮር
-
በቁርጠኝት መስራት
አጠቃላይ የጥራት መርሆዎች
-
ለተገልጋዩ ህብረተሰብ በትህትና አገልግሎት እንሰጣለን
-
ለዜጎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ፈጣን መልስ እንሰጣለን
-
ላስቀመጥነው እሴቶች እንገዛለን
የተገልጋዮች መብት
-
ባስቀመጥነው የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት በክብር የማስተናገድ
-
የጠየቁትን ጥያቄ ቶሎ መልስ የማግኘት
-
ቅሬታና አስተያየት የማቅረብ
-
ላቀረቡት ቅሬታ ፍትሃዊ ምላሽ የማግኘት
-
ልዩ ትኩረት የሚሹ የህዝብ ከክፍሎች በልዩ ትኩረት የመስተናገድ ና አገልግሎት የማግኘት
-
በቂና ወቅታዊ ምላሽ ባጡበት ጊዜ ለሚዲያ ወይም ለሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ኣካላት የማሳወቅ
በተቋሙ የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
-
የካሳ ምትክ ቤት ወይም ምትክ ቦታ መቀበያ የተነሺነት ምስክር ወረቀት አገልግሎት
-
ምትክ ቦታ የመስጠት አገልግሎት (ለግል ይዞታ ተነሺና ለንግድ ቤት ተከራይ ተነሺ ለሆነ)
-
ምትክ ቤት የመስጠት አገልግሎት
-
የሊዝ ውል ማዋዋል አገልግሎት እና ማህደር መክፈትና የማደራጀት ስራ
-
ለተነሺ ባለ ይዞታዎች ካሳ ክፍያ የመስጠት አገልግሎት
-
የከተማ መሬት ይዞታ ማረጋገጫ (የሊዝ ይዞታ ማረጋገጫ) የምስክር ወረቀት የመስጠት አገልግሎት
-
የከተማ መሬት የነባር ይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የመስጠት አገልግሎት
-
የቦታ የመጠቀም መብት ለሽያጭ ወይም በስጦታ ወይም በውርስ የማስተላለፍ አገልግሎት
-
የድንበር ክርክር መፍታት አገልግሎት
-
ይዞታ የመክፈል አገልግሎት
-
ይዞታ የመቀላቀል አገልግሎት
-
የእዳና እገዳ የመመዝገብ አገልግሎት (ለግንባታ ፍቃድም ሆነ ለውልና ማስረጃ)
-
የይዞታ ሰነድ ህጋዊነት የመማረጋገጥ እና ማስረጃ የመስጠት አገልግሎት
-
ምትክ ካርታ (ደብተር ኮፒ) የመስጠት አገልግሎት
የአገልግሎት አይነት
-
የከተማ መሬት የነባር ይዞታ ማረጋገጫ የምስክር
-
የቦታ የመጠቀም መብት በሽያጭ/በስጦታ ወይም በውርስ የማስተላለፍ አገልግሎት
-
የድንበር ክርክር መፍታት አገልግሎት
-
ይዞታ የመክፈል አገልግሎት
-
ይዞታ የመቀላቀል አገልግሎት
-
ዕዳና እገዳ የመመዝገብ አገልግሎት
-
ምትክ ካርታ/ደብተር ኮፒ የመስጠት አገልግሎት
-
ለግንባታ ፍቃድ የዕዳና እገዳ አገልግሎት
-
ለውልና ማስረጃ የዕዳና እገዳ አገልግሎት
