Thursday, April 30, 2026

የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ

መግቢያ

ዘመናዊና የተደራጀ የከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባ ስርዓት ዝርጋታ ውሱን የሆነውን የከተማ መሬት በተገቢው መንገድ ለተገቢው አገልግሎት ለማዋል ወሳኝ ነው፡፡ ይኸውም የህብረተሰቡን የይዞታ ተጠቃሚነት ዋስትናን በማረጋገጥና የመሬትና መሬት ነክ ንብረት ግብይቱን በማቀላጠፍ የከተሞች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ይቻላል፡፡
በመሆኑም መንግስት የመሬት ይዞታ መረጃ በተሟላ መልክ መኖር በተለይ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱን ይበልጥ የተሳለጠና ውጤታማ ማድረግ እንደሚያስችል በመረዳት በዘርፉ የተስተዋሉ ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ይቻል ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ተሰቶት ለተግባራዊነቱ ወጥና የተደራጀ  አሰራርና አደረጃጀት በመፍጠር ወደስራ ተገብቱዋል፡፡

የኤጀንሲው ራዕይ

በሐረር ከተማ ዘመናዊ የመሬት ይዞታ መረጃ ምዝገባ ስርዓት ተዘርግቶ በዘርፉ አስተማማኝ ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ፣ ውጤታማ አገልግሎት የሚሰጥበት፣ ተጠቃሚውን ያረካና አመኔታ የተጣለበት ተቋም ሆኖ ማየት ፡፡

የኤጀንሲው ተልእኮ

በሐረር ከተማ ውስጥ ዘመናዊ፣ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ የካዳስተር፣ የመሬት ይዞታ ተጠቃሚነት፣ የመሬት-ነክ ንብረት ባለቤትነት ምዝገባና መረጃ ዋስትና የሚሰጥ ሥርዓት መገንባት እንዲሁም ቀልጣፋ፣ጥራት፣ ግልጸኝነትና ተጠያቅነት ያለው የመሬት ይዞታ ምዝገባ አገልግሎት በመስጠት ለዜጎች ፣ ለግል ዘርፍ ፣ ለመሬት አመራር ፣  አስተዳደርና መሬት-ነክ ንብረት ዋጋ ግመታ የሚሆን ከህጋዊ ካዳስተር ስርዓት የመነጩ መረጃዎችን በመስጠት ለኢኮኖሚያዊ እድገት መፋጠን አስተዋጽዖ እንዲኖር ማድረግ፤

የኤጀንሲው ስልጣንና ተግባራት

በአዋጅ ቁጥር 818/2006 መሠረትኤጀንሲው ለከተማ ልማት እና ኮንስተራክሽን ቢሮ ተጠሪ ሲሆን የሚከተሉት ተግባራትና ሀላፊነቶች ይኖሩታል ፡፡
  1. የከተማውን የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ አጠቃላይ ሥራዎችን ይከታተላል፣ይመራል፣ያስተዳድራል፣
  2. በምዝገባ ሕግ መሠረት የመሬት ይዞታ ምዝገባን በተመለከተ የካዳስተር፣የመብት እና ገደቦች መረጃን ከመብት ፈጣሪ ተቋም በመቀበል ይመዘግባል፣የመብት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት`ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያስተካክላል፣ ይሰርዛል፤ ደህንነታቸውን ይጠብቃል፤ እንዲሁም ያስተዳድራል፡፡
  3. የካዳስተር ካርታ ያዘጋጃል፣ወቅታዊ ያደርጋል፣
  4. ለስልታዊ ዘዴ ይዞታ ማረጋገጫ ፕሮጀክት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡
  5. የተመዘገበውን የመሬት ይዞታ የምዝገባ ውጤቶችን በመረጃ ቋት ይይዛል፣ያስተዳድራል፣ ይተነትናል፣ ወቅታዊ ያደርጋል፤እንዲሁም መረጃ ይጠቀማል፣ ይሰጣል፡፡
  6. የመሬት ይዞታ ተጠቃሚነት መብት የተሰጠው ሰው በእያንዳንዷ ቁራሽ መሬት ያለውን መብት ፣ክልከላ እና ሀላፊነቱን የሚገልጽ ሰነድ በወረቀት ወይም በወረቀት እና በድጅታል ፎርም ያዘጋጃል፡፡
  7. ከመሰረታዊ ካዳስተር ካርታ ፣የካዳስተር ማውጫ ካርታ እና ከሀገራዊ የጂኦደቲክ ቅየሳ መረብ በመነሳት ካዳስተር ካርታ በወረቀትና በድጅታል ፎርም  ያዘጋጃል፣ወቅታዊ ያደርጋል፣
  8. ከሚመለከተው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የሐረር ከተማ ህጋዊ ካዳስተር መረጃ ሥርዓት ላይ መደበኛ የሆነ የስጋት እና የደህንነት ቁጥጥር ያደርጋል፣
  9. የካዳስተር ቅየሳ ስራዎች ያከናውናል
  10. ለካዳስተር ቅየሣ አስፈላጊ የሆኑ አዲስ የመሬት መቆጣጠሪያ ነጥቦች በሚቋቋሙበት ወይም የነበረው የሚታደስበትን ሁኔታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ይሠራል ፡፡
  11. በክልሉ ካዳስተር መረጃ ሥርዓት ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችንና ለቅልጥፍና እና ጥቅም ላይ መዋል የማይችሉትን አሰራሮች ለማስቀረት የሚያስችል ቀጣይነት ያለው ማሻሻያና ለውጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ያደርጋል፡፡
  12. የሕጋዊ ካዳስተር መረጃን ለህዝብ ክፍት ያደርጋል፣
  13. ከሐረር ከተማ ካዳስተር መረጃ ስርአት ጋር በተያያዘ የመረጃ ቴክኖሎጂ የመምራትና የማስተዳደር ስራዎች ያከናውናል፡፡
  14. ተግባራቱን በሚመለከት በፌዴራል ደረጃ የሚወጡ አግባብነት ያላቸውን ህጐች ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ያስፈጽማል፡፡
  15. መሻሻል ያለባቸውን ህጐችና አሠራሮች እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፣ ሲፀድቁም ተግባራዊ ያደርጋል፡
  16. ተግባሩን በሚመለከት የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ይመረምራል፣ ውሳኔም ይሰጣል፣
  17. በህግ መሠረት የአገልግሎት ክፍያ ይሰበስባል፣
  18. የሚሰሩ ሥራዎች እና የሚሰጡ አገልግሎቶች ግልጽነት ያለውና ፈጣን እንዲሆኑ የሚያስችል የሥራ ማንዋል እና የአቅም ግንባታ ኘሮግራም ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ያዘጋጃል፣
  19. በሥልታዊ ዘዴ ወይም እንደአስፈላጊነቱ በአልፎ አልፎ ዘዴ የመሬት ይዞታን የማረጋገጥ ሥራዎችን ያከናውናል፤በውጤቱም መሰረት ምዝገባ ያደርጋል፣
  20. በካዳስተር እና ከተማ ኘላን መረጃ መሠረት የመሬት ይዞታ መካፈልንና መቀላቀልን ይመዘግባል፣
  21. መመዝገብ ያለባቸውን የመሬት ይዞታዎች ልዩ መለያ ኮድ ይሰጣል፣
  22. ህጋዊ ካዳስተር መረጃ ሥርዓት መረጃ ይይዛል፣ ወቅታዊ ያደርጋል፣እንዲሁም መረጃ ይጠቀማል፣ መረጃ ይሰጣል፣

የመሬት ይዞታ ማረጋጋጥ ምንነትና ዘዴዎች

የመሬት ይዞታ ማረጋጋጥ ማለትየአንድ ይዞታ ሰነድ ላይ ያለው የመብት መረጃ ከይዞታው ወሰን ላይ በኦርቶ ፎቶ ወይም በምድር ቅየሳ ዘዴ ከተሰበሰበው መረጃ ጋር የተመሳከረና ሁለቱ መረጃዎች በልዩ መለያ ኮድ ተሳስረው ባለይዞታው፣ በይዞታው ላይ ለውን መብት፣ ክልከላና ሃለፊነት በግልፅ የሚያሳይ ሆኖ የሚደራጅበት ነው፡፡ ሁለት አይነት የይዞታ ማረጋገጥ ዘዴዎች ሲኖሩ እነሱም ስልታዊ እና አልፎአልፎ የይዞታ ማረጋገጫ ዘዴ ናቸው፡፡

የከተማ መሬት ማረጋገጥና ምዝገባ አላማዎች፣

  • በከተማ መሬት ይዞታ ላይ ያለን መብት፣ ክልከላና ሃላፊነትን በመመዝገብ የባለይዞታውን የይዞታ ተጠቃሚነት ዋስትና በመስጠት እና በይዞታው ላይ ላረፈ የማይንቀሳቀስ ንብረት የባለቤትነት መብት እውቅና እንዲኖረው ማስቻል፤
  • የከተማ መሬት ይዞታን መመዝገብና ዋስትና መስጠት ዜጎች ሃብታቸውን ልማት ላይ እንዲያውሉ በማበረታታቱ የከተሞችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊ እና አካባቢያዊ ልማትን በማፋጠን የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ማስቻል፤
  • የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ ለማንኛውም ባለይዞታ በይዞታው የመጠቀም መብቱ ወጥ በሆነ ደረጃ የሚያስጠብቅና ከተሞች ያላቸውን መሬት ቆጥረው ማወቅ እንዲችሉ ማድረግ፤
  • በሀገር አቀፍ ደረጃ ተናባቢ የሆነ የመሬት ይዞታ መረጃ እንዲኖር እና አሠራሩ ከገጠር የመሬት ይዞታ አስተዳደር ጋር ተጣጥሞ አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመገንባቱን ሂደት ማገዝ ማስቻል፤
  • በዘርፉ የውሳኔ አሰጣጡን ማቀላጠፍና ማገዝ ማስቻል፣ በዘርፉ ሁሉም ሰው ግልጽነት የሚፈጠርበት የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት፤
  • አንድ ሰው በመሬት ይዞታው ላይ ያፈራውን ሃብት በዋስትናነት በማስያዝ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ፤
  • ለኢኮኖሚ እድገቱ ቁልፍ ሚና ለሚጫወተው ለመሬት ነክ የንብረት ገበያና ለባለይዞታዎችም ጭምር አስፈላጊ የሆኑ የከተማ መሬት ይዞታ መረጃዎችን በተሳለጠ ሁኔታ ለመስጠት፤
  • የመሬት ይዞታውን አስመልክቶ የሚነሳ ክርክር በመቀነስ ህብረተሰቡ ጊዜውን ለስራ የሚጠቀምበት አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የከተማ መሬት ማረጋገጥና ምዝገባ መርሆዎች፣

የከተማ መሬት ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ተግባራት በሚከናወኑበት ወቅት ከዚህ በታች የተገለፁ ዋና ዋና መርሆዎችን ግምት ውስጥ ያስገባና ያከበረ መሆን ይኖርበታል፡፡
እነሱም፡-
  • ሂደቱ በይዞታው ላይ ያለን መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት አስቀድሞ ተረጋግጦ የሚመዘገብበት በመሆኑ የባለይዞታው መረጃ ከመሬት አስተዳደር መረጃ ጋር ተመሳሳይ መሆን ይኖርበታል፤
  • ማንኛውም የይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ውጤት በይዞታው ላይ ቀደም ብሎ በህግ ስልጣን በተሰጠው አካል የተሰጠ መብትን ህጋዊነት አረጋግጦ ከመመዝገብና በተመዘገበ ይዞታ አገልግሎት ከመስጠት በስተቀር በይዞታው ላይ ምንም ዓይነት መብት የሚፈጥር፣ የሚያሰቀር፣ የሚቀንስ፣ የሚጨምር፣ የሚለውጥ ወይም የሚያሻሽል መሆን የለበትም፡፡
  • የከተማ መሬት ይዞታ ማረጋገጥ፣ ምዝገባና አገልግሎት አሰጣጥ ስራ በሚተገበርበት ወቅት የሴቶችን፣ የአካል ጉዳተኞችንና የወጣቶችን ተሳታፊነትና ባለይዞታ የሆኑትን ተጠቃሚነታቸውን ባረጋገጠ መልኩ መሆን አለበት፤
  • መብት ጠያቂው ያቀረበው ሰነድ ለማረጋገጥ ሂደት ብቁ ካልሆነ ስልጣን ባለው አካል የመሬት ይዞታው ትክክለኛነት ተረጋግጦ መቅረብ አለበት፤
  • የማንኛውም ሰው ግልጽ የሆነ የመሬት ይዞታ መብት፣ ክልከላ እና ሃላፊነት ይመዘገባል፤
  • ማንኛውም በመሬት ይዞታ ላይ ያለ መብት ክልከላና ኃላፊነት የሚመዘገበው የይዞታ ማረጋገጥ ሂደትን ሲያልፍ ብቻ ነው፡፡

Follow Us

3,854FansLike
5,574FollowersFollow
6,324SubscribersSubscribe

All Land holding registation Post

All Land holding registration Post

‎የሐረር ከተማ የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት ሙከራ በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ።

የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከሐረሪ ብ/ክ/መ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ጋር በመሆን በሐረር ከተማ የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት በመተግበር ላይ ይገኛል። ‎ ‎የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል...