የመሬት ይዞታ መረጃና ምዝገባ ኤጀንሲ በመንገድ ዳር ለሚተከሉ የሰፈር እና የመንገድ ላይ ቁጥር መለጠፊያ ምሶሶዎችን በከተማችን ዋና ዋና መንገዶች ላይ የመትከል ስራ እየተሰራ ይገኛል ።
በተተከሉት ፖሎች ላይ የሰፈሮቹ ዲጂታል አድራሻ ቁጥር በቀላሉ ከሩቅም ከቅርብም በሚታይ መልኩ በሰማያዊ እና በአረንጓዴ ቀለም ታፔላ የታሰረ ሲሆን ሰማያዊው ታፔላ የሰፈር /Neighborhood / ቁጥሮችን የሚያሳይ ሲሆን በተጨማሪም በየሰፈሩ ውስጥ የሚገኙትን የቤት ቁጥር Range ከስንት እስከ ስንት እንደሚገኝ ይጠቁማል። አረንጓዴው ታፔላ በተመሳሳይ መንገዶችን አድራሻ የሚጠቁም ሆኖ ከ Principal Arterial ዋናው ከአዲስ አበባ ወደ ጂግጂጋ የሚሄደው የፌደራል መንገድ አንስቶ በከተማው ውስጥ የሚገኙትን ሁሉንም የመንገድ አይነቶች የሚያመላክት ይሆናል ። በመሆኑም ጎዳና/Avenue /፥ መንገድ /Street/፥ ንኡስ መንገድ /Sub Street/፥ የግል መንገድ/Private Road/፥ እንዲሁም የዘላቂ ያልሆኑ/Cul da sacs/ መንገዶችን የሚያመላክት ይሆናል።
በከተማችን እየተተገበረ የሚገኘው የዲጂታል አድራሻ ስርአት ትግበራ እንደሚታወቀው በተመረጡ ሰፈሮች ውስጥ የቤት ቁጥር የመለጠፍ ስራ የተከናወነ ሲሆን ፤ ባለይዞታዎች እንዲሁም እንግዶች እነዚህን አድራሻዎች በመጠቀም በቀላሉ የተለያዩ አገልግሎቶችን የቱሪስት መዳረሻዎችን ፣ የግብይት ፣ የናቪጌሽን፣ የመንገድና አቅጣጫን የመለየት፣ የባንክ አገልግልት ፣ የፍሳሽ አገልግልት፣ የመብራት፣ የውሃ አቅርቦት አገልግልት፣ የሆስፒታል፣ የፖሊስ፣ የእሳት አደጋ መከላከል ፣ የአምቡሊንስ፣ እና ሌሎች በርካታ አገልግሎቶች ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል ።






