Thursday, April 30, 2026
HomeNews & EventLand holding registration agencyበከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ይዞታ መረጃና ምዝገባ ኤጀንሲ የከተማ ቦታ ኪራይና...

በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ይዞታ መረጃና ምዝገባ ኤጀንሲ የከተማ ቦታ ኪራይና የከተማ ቤት ግብር የ2017 አፈጻጸም ውይይት እና የ2018 በጀት አመት እቅድ ዙሪያ በጋራ ለመስራት ከባለድርሻ አካላት ቴክኒካል ባለሙያዎች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል ።

የገቢዎች ባለስልጣን ኃላፊ አቶ ያሲን አብዱላህ የመክፈቻ ንግግር አድገዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ከፍተዋል ። አቶ ያሲን የስልጠና መድረኩን ስከፍቱ በ2018 በጀት ዓመት የተለጠጠ የገቢ ዕቅድ መያዙን ገልፀው ዕቅዱ እንዲሳካ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት አለባቸው በማለት ገልጸዋል ።

የመሬት ይዞታ መረጃና ምዝገባ ኤጀንሲ ሃላፊ አቶ ኢብራሂም አህመድ እንደገለፁት የስልጠናው አስፈላጊነትን በተመለከተ የ2018 ዕቅድ የበለጠ በውጤታማነት ለመፈጸም በሶስቱ (በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ፤ በገቢዎች ባለስልጣን ና ማዘጋጃ ቤት)ተቋማት መካካል በ2017 በጀት አመት የነበረውን ቅንጂታዊ አሰራር ይበልጥ በቴክኒካል ባለሙያዎች ዘንድ በማጎልበት መስራት የሚያስፈልግ መሆኑን በመግለጽ የዛሬው ስልጠና ይህ እንዲዳብር ወሳኝ ነው ብለዋል ። አክለውም የከተማ ቦታ ኪራይና የከተማ ቤት ግብር ገቢ አሰባሰብ ያጋጠማቸው ችግሮችን በመለየት ለቀጣይ የ2018 በጀት አመት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ መሆኑንም ገልጸዋል ።

በመድረኩም የከተማ ቦታ ኪራይና የከተማ ቤት ግብር የ2017 አፈጻጸም በአቶ ሻምበል አስፋው ቀርቧል ። በቀረበው ሰነድ ዙሪያም በመድረኩ የተገኙ ባለሞያዎች አስተያየት እና ጥያቄዎች በማንሳት ተወያይተው በመጨረሻም የስራ አቅጣጫ አስቀምጧል ።

ሐምሌ 25/2017 ዓ.ም

RELATED ARTICLES

Most Popular

Recent Comments