የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በሀረር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በመገኘት በመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የተከናወኑ የካዳስተር እና የአድራሻ ስርአት ስራዎችን ጎበኙ ።ሚኒስትሯ በመስክ ምልከታው የሀረር ከተማን ስማርቲ ሲቲ በማድረግ ለማህበረሰቡ ግዜውን የዋጀ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ለመስጠት የተኬደበት ርቀትም የሚያስመሰግን መሆኑን ተናግረዋል።በጉብኝቱ ላይ ሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ኡመር ፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙኽታር ሳሊህ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።



