በከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ የዲጂታል አድራሻ ስርአት ትግበራ ዙሪያ ተግባራዊ ስልጠና ለመረጃ ሰብሳቢዎች እና ለአስተባባሪዎች መስጠት የተጀመረ ሲሆን ስልጠናውም ከስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሺያል ኢንስቲትዩት የDAS project ኃላፊ አቶ አግማሴና የቡዱኑ ከፍተኛ ባለሞያዎች እየተሰጠ ይገኛል ።
ከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ቢሮ ከየስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አስቻይ መሠረተ ልማት የሆነውን የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት ለመተግበር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። ዲጂታል የአድራሻ ሥርዓት ማለት ማንኛውም በከተማው ወሰን ውስጥ የሚገኙ ቤቶችን፣ መንገዶችን፣ ልዩ ልዩ ተቋማት እና ቦታዎች ያሉበትን መገኛ ቦታ፣ ርቀትና አቅጣጫ በቀላሉ ለማወቅ የሚያስችል (Addressing) እና መንገድ እየመራ የሚወስድ (Navigation) ቴክኖሎጂ ነው። ይህም አንድ ሰው የቤቱን ቁጥር ወይም ዲጂታል አድራሻ ብቻ በመጠቀም ያለማንም ርዳታ በቀላሉ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ እና የተለያዩ አገልግሎቶችን ለመስጠት ወይም በአለበት ቦታ ሁኖ አገልግሎቱን ለማግኘት ያስችለዋል። ዲጂታል የአድራሻ ሥርዓት ፋይዳ ፡ቀልጣፋና አስተማማኝ የፖስታ፣ የትራንስፖርት እና የእቃ የማድረስ (Delivery) አገልግሎት እንዲኖር ያስችላል፤ ኤሌክትሮኒክስ ግብይት ለመፈጸም እና የቤት ለቤት እቃ ለማድረስ ፤ ተሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር (Fleet management) ፤ የመሬት ካዳስተር ምዝገባ እና ቁጥጥር ሂደትን ይደግፋል ፤ የመሬት ሊዝ ሂደትን ቀልጣፋ ያደርጋል፤ የመንግስት/ቀበሌ ቤቶች የኪራይና የአስተዳደር ስራን ያዘምናል ፤ ከተማችንለኢንቨስትመንት ተመራጭ ከተማ ያደርጋታል፤ የስራ እድሎችንም ይፈጥራል ፤ የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት ቀልጣፋና ምቹ እንዲሆን ያስችላል ፤የሚያጋጥሙ የመኪና ግጭቶችንና አደጋዎችን በፍጥነት ለመፍታት (incident management)፤ የትራንስፖርት ተገልጋዮች የሚያወጡትን የነዳጂ ወጪ፣ የሚያባክኑትን ጊዜ፣ ጉልበት እና ገንዘብ እንዲቆጥቡ ያስችላቸዋል ፤ ፈጣን የህክምና ርዳታ ለመስጠት ፤ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ፤ የጎርፍ አደጋ፤ መሰል አደጋዎች በሚያጋጥም ጊዜ ፈጣን ምላሽ እና ድጋፍ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። ከተማ አስተዳደሩ የንግድ ፍቃድ ለመስጠትና ለማሳደስ ፣ ግብር በቀላሉ ለመሰብሰብና ለማዘመን ያስችላል። መሠረተ ልማት ለመዘርጋትና ለማስጠገን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ፣ የህዝብና ቤት ቆጠራ ስራዎችን ያዘምናል፤ በከተማው ውስጥ የሚደረጉ የቱሪስት እንቅስቃሴዎችን ያቀላል፤ የቱሪዝም ዘርፉን ያሳድጋል፤ ምቹና ዘመናዊ ከተማና ንቁ ማህበረሰብ (Smart City & Smart Society) ለመገንባት፤ የዲጂታል ኢኮኖሚ እውን ለማድረግ ያስችላል።
ስልጠናው ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት በተግባር መስክ ላይ እንደሚቀጥልም ከስልጠናው አዘጋጅ መሬት መረጃና ምዝገባ ኤጀንሲ የዲጂታል አድራሻ ስርአት ፐሮጀክት አስተባባሪ ለማወቅ ተችሏል።









