Thursday, April 30, 2026
HomeNews & Eventብልፅግና ፓርቲ የህዝባችን አዳጊ ፍላጎቶችን በማሳካት እና ተግዳሮቶችን በመቀነስ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ...

ብልፅግና ፓርቲ የህዝባችን አዳጊ ፍላጎቶችን በማሳካት እና ተግዳሮቶችን በመቀነስ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ሲሉ የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ተናገሩ

የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በክልሉ አገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ከከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ ። የውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ እንደተናገሩት በክልሉ የህዝባችን አዳጊ ፍላጎቶችን በማሳካት እና ተግዳሮቶችን በመቀነስ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። ፓርቲያችን የረጅም ጊዜ ርዕይ በማለም አገልግሎት አሰጣጣችንን በማዘመን ዜጎችን ዜጎች ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ሀገራችንን ወደ ፊት ለማስፈንጠር እየተጋ ይገኛል ብለዋል ። በተለይም መዲናችን ሐረር ከተማ አዲስ የከተማ ልማት ስትራቴጂ በመንደፍ ከተማዋን በፕላን እንድመራ የተለያዩ ስራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ አንሰተዋል ። ይህንን የፕላን እስትራቴጂ ተግባራዊ ለመድረግ ህግና ስርአት በተከተለ ሁኔታ መመራት ያስፈልጋል ብለዋል ።የሐረሪ ክልል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙኽታር ሳሊህ በበኩላቸው በበጀት አመት በክልሉ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል ። ሀረር ከተማ በኘላን እንድትመራ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየቱን አንስተው ለኢንቨስትመንት የሚውል መሬትን ከማስተላለፍ አንጻር የነበሩ አካሄዶች በመቀየር ፍትሃዊነትን ማረጋገጥ የሚያስችል አሰራር መጀመሩን ገልፀዋል ። ህገወጥ የመሬት ወረራና ግንባታ ከመከላከል አንፃር በስፋት መሰራቱን ጠቁመው በቀጣይም ህገወጥ ግንባታንና የመሬት ወረራን ለመከላከል ሁሉም በቁርጠንነት መረባረብ ይኖርበተል ብለዋል። ከመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዘው ሪፖርት ያቀረቡተ የክልሉ ፓብሊክ ሰርቪስ ኃላፊ ወይዘሮ ዚነት ዩሱፍ የተቋማት አሰራርን በማዘመን ተደራሽነትን ፣ ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ፣ ሌብነትን በመቀነስ የዜጎች እርካታን ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

RELATED ARTICLES

Most Popular

Recent Comments