Thursday, April 30, 2026
HomeNews & EventMeetingበዛሬው እለት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመልካም አስተዳደር ትግበራና መርሆችን ለቢሮው ሠራተኞች...

በዛሬው እለት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመልካም አስተዳደር ትግበራና መርሆችን ለቢሮው ሠራተኞች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰቷል።

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ም/ል ቢሮ ሀላፊ አቶ ረኢስ ዩሱፍ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ስልጠናውን አስጀምረዋል ። መልካም አስተዳደር መርሆዎች ፣የሰራተኛው ስነ ምግባር ጋር የተያያዙ 12 ኮዶች እንዲሁም የቅሬታ ና የአገልግሎት እስታንዳርድ እንደሚሰጥ ገልጸዋል። በዋናነት በተቋማችን የተገልጋይ እርካታ እንዴት ማሳደግና ማሻሻል እንደሚገባ፣ ብልሹ አሰራር እንዴት መቅረፍ እንደሚቻል እንዲሁም ያሉትን ችግሮች ከመቅረፍ ጋር የተያያዘና እነዚህን ጉዳዮች ያካተተውን እቅድ በአግባቡ መተግበር እንደሚገባ ም/ል ቢሮ ሀላፊ አቶ ረኢስ ዩሱፍ ገልፀዋል።
በመልካም አስተዳደር ትግበራና መርሆች የዜጎች እርካታ ለማረጋገጥ እንዲችል በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት ተቋማት እና የመልካም አስተዳደር ሚና ያላቸው ሌሎች አካላት የመልካም አስተዳደር ምንነት ባህሪያት እና ተያያዥ ያደረገ ግንዛቤና እውቀት መኖር እንዳለበት የመጀመሪያውን ሰነድ ያቀረቡ የተቋሙ የለውጥና የመልካም አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ሸኪብ አብዱረህማን ገልፀዋል ።
በመቀጠልም ስለ ሰራተኞች ስነምግባር 12 ኮዶች አስፈላጊነት የመንግስት ተቋማት ና ሰራተኞች የሚመሩበት የስነምግባር መርሆዎችን ስራ ላይ በማዋል በስነምግባሩ የተመሰገነና በአቅሙ የጎለበተ የመንግስት ሰራተኛ ለማፍራት ነው በማለት የማስፈፀም አቅም ግንባታ ማስተባበሪያ ዪኒት ዳይሬክተር አቶ አብዲ መሀመድ ገልጸዋል ።
በስልጠናው የመልካም አስተዳደር ትግበራና መርሆች እና የሰራተኛው ስነ ምግባር ኮድ በተመለከተ በቀረበው ሰነድ ዙሪያ በስፋት ውይይት ተካሂዷል ።
RELATED ARTICLES

Most Popular

Recent Comments