Thursday, April 30, 2026
HomeNews & EventDevelopmentየሀረር ከተማ ዲጂታል አድራሻ ስርአት ትግበራ በሐረር ከተማ 1548 መንገዶች አዲስ እና...

የሀረር ከተማ ዲጂታል አድራሻ ስርአት ትግበራ በሐረር ከተማ 1548 መንገዶች አዲስ እና ዘመናዊ የአድራሻ መለያ ቁጥር እየተሰጣቸው ይገኛል:

በሐረር ከተማ ስያሜ ያልተሰጣቸው 1548 መንገዶች አዲስ እና ዘመናዊ ዲጂታል የአድራሻ መለያ ቁጥር እየተሰጣቸው ይገኛል።

በሐረር ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የአድራሻ ሥርዓት ዝርጋታ እና አስተዳደር እንደገለፀው በከተማዋ 1548 መንገዶች ምንም አይነት ስያሜ እና ቁጥር ያልተሰጣቸው እንደሆኑ ጠቅሰው፤ በአዲስ ዲጂታል የአድራሻ ሥርዓት መሰረት ስያሜና መለያ ቁጥር እንደሚያገኙ ተገልፃል። በተጨማሪም ከመንገዶቹ ጋር ትስስር ላላቸው 10 ሺህ ቤቶች አዳዲስ የቤት ቁጥር እንደሚሰጣቸዉ ገልጸው እስካሁን ከ600 በላይ ቤቶች ላይ የቤት ቁጥር የመለጠፍ እና በ110 መንገዶች ላይ (አቅጣጫ ጠቋሚ) ታፔላ የመስቀል ሥራ ተሰርቷል ብለዋል።

ከተማችን ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የዲጂታል አድራሻ ስርአት እንዲኖራት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ከኢትዮጵያ ጂኦስፓሺያል እና ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ጋር በ2016 ግንቦት ወር ላይ የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም በ2017 በጀት አመት በመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ስር የዲጂታል አድርሻ ስርአት ትግበራ አስተባባሪ ቡድን በማደራጀት ወደ ተግባር መገባቱ ይታወቃል። ዲጅታል የአድራሻ ሥርዓት የቦታዎችን አቅጣጫ፣ ርቀትና የትራፊክ እንቅስቃሴን እንዲሁም ሌሎች በርካታ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳዎች ያሉዋቸው ሲሆን በተለይ ከተማችን የቱሪስት መዳረሻ እንደመሆኗ መጠን አንድን ቦታ በቀላሉ ያለምንም መጉላላት ማግኘት እንዲቻል ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል:

በመሆኑም እየተተገበረ ያለው የዲጂታል አድራሻ ስርአት ፐሮጀክት አፈፃፀም በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ሲሆን በሀገር አቀፍ እንዲሁም በክልል/በከተማ ደረጃ ምቹ እና የዘመናዊ ከተሜነት እና የዘመናዊ ማህበረሰብን /smart city and smart society/ ለመገንባት እየተደረገ ያለውን ጥረት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድግ ብሎም የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ የሚያቀል እና የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያሻሽል እንደሚሆን ይጠበቃል።

በከተማችን ውስጥ 17 ጎዳናዎች ፤ 62 መንገዶች ፥ 20 ንኡስ መንገዶች፥ 850 ፓዝ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፥489 ዘላቂ ያልሆኑ/ውስን / መንገዶችን፥ 110 የግለሰብ መንገዶች ባጠቃላይ 1548 መንገዶች በኮድ(ቁጥር) ተሰይመዋል። 1029 የታዋቂ ቦታዎች መረጃዎች (ኢንሹራንሶች፥ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፥ ሆቴሎች ፥ ሆስፒታሎች ፋርማሲዎች ፥የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ታሪካዊ ቦታዎች ፥ የሀይማኖት ተቋማት የመንግስት ተቋማት ፥ ፖሊስ ጣቢያዎች ባጠቃላይ የፀጥታ ተቋማት ፥ . . .) መረጃ ተሰብስቦ ወደ ሲስተም ገብቷል።

ዲጅታል የአድረሻ ስርዐቱን ተግባራዊ ለማድረግ በጂኦስፓሺያል እና ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት የለማ መተግበርያ (አኘሊኬሽን) በአሁኑ ወቅት ስራው ተጠናቅቆ በሙከራ ላይ የሚገኝ ሲሆን መተግበሪያው አራት ቋንቋዎችን የሚሰራ ሆኖ ሐረሪ ፤ ኦሮምፋ ፤ አማርኛ እንዲሁም እንግሊዝኛ ቋንቋን በመጠቀም አድራሻዎችን መፈለግ ያስችላል፤ የከተማችን የዲጂታል አድራሻ ስርዐት ፥ መሬት ላይ መቆጣጠሪያ ነጥቦችን ፥ የመንገድ ላይ ካሜራዎችን ሲሲቲ/ ካሜራ/፥ ከከተማ ውጪ ሶስቱ ገጠር ወረዳዎች የሚገኙ ዋናዋና መንገዶች እና የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ ሲስተም መግባታቸው ከሌሎች ከተሞች በተለየ ያደርገዋል።

RELATED ARTICLES

Most Popular

Recent Comments