Thursday, April 30, 2026
HomeMeetingCommunityየከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በኮሪደር ልማት የህንፃ እና...

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በኮሪደር ልማት የህንፃ እና ግንባታን በማስዋብ (Facade) ስታንደርድ ማስጠበቅና የኮሪደር ልማት ግንባታ በተመለከተ ከወረዳ አመራሮች ፤ከፀጥታ ዘርፍ እና ከፖሊስ ኮሚሽን ጋር ውይይት አካሂዷል ።

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙኽታር ሳሊህ፣ የክልሉ የፍትህና ፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ቶፊቅ መሐመድ እና ከወረዳ አመራሮች ፤ከፀጥታ ዘርፍ እና ከፖሊስ ኮሚሽን ጋር በውይይት መድረክ ተገኝተዋል ።

በኮሪደር ልማት የህንፃ እና ግንባታን በማስዋብ (Façade) ስታንደርድ ማስጠበቅና የኮሪደር ልማት ግንባታዉ ላይ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከሁሉም ወረዳዎች ፣ከፀጥታው ዘርፉ ከፖሊስ እና ከሚኒሻ ጋር በጋራ በመሆን በመቀናጀት መስራት እንደሚገባ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙኽታር ሳሊህ ገልጿል ።

የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ሃላፊ አቶ መሐመድ ኑረዲን የህንፃ እና ሌሎች ግንባታዎችን የማስዋብ (Façade) ስታንደርድ ማስጠበቅ ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ አቅርቧል ።

የኮሪደር ልማት ስራ በከተማችን በጥሩ ሁኔታ አስደማሚ ለውጦችን እያሳያ የሚታይ በርካታ ስራዎች ተከናውኗል። በመሆኑም የከተማ ገፅታን ለመጠበቅና የአካባቢውን ደረጃ የሚያሳድግ ስታንዳርድ እና ዲዛይኖችን በመጠበቅ የግል ይዞታዎች ፣ የንግድ ተቋማትን እንዲሁም ህንፃዎች ወጥ የሆነ መንገድ በማድረግ እና በአከባቢው ከደረጃ በታች የሆኑ ይዞታዎችን በመልሶ ማልማት ሂደት ውስጥ የሚለማበት አማራጮችም በመጠቀም ሁሉም ወረዳዎች ፣ከፀጥታው ዘርፉ ፣ከፖሊስ እና ከሚኒሻ ጋር በጋራ በመሆን እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላትና አስፈላጊው የባለሙያ ድጋፍ በጨመር በተቀመጠው የግዜ ገደብ ውስጥ ለማጠናቀቅ በርብርብ እንዲከናወን አሳስበዋል።

የከተማ ገፅታን የማስዋብ ስራ ለአከባቢው ነዋሪ ብሎም ለከተማው ዕድገት የሚኖረው አስተዋፆ ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ የድርሻውን ተሳትፎ እንዲያደርግ እንዲሁም የህንፃ እና ሌሎች ግንባታዎችን የማስዋብ (Façade) ስታንደርድ ስራ ወይም የተቀመጠው መመሪያውን ተግባራዊ በማያደርጉ ለልማቱ ስራ እንቅፋት በሚሆኑት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ በማለት የፍትህና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ቶፊቅ መሀመድ በውይይቱ ገልፀዋል።

በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ በመድረኩ ላይ የተገኙት ተሳታፊዎች ጥያቄ እና አስተያየታቸውን በማቅረብ በሰፋት ተወያይተዋል ።//***

RELATED ARTICLES

Most Popular

Recent Comments