ውይይቱ ከሻሽ – ቢራ – እንደራሴና ጁኔር ኮሪደር ልማት የህንፃ እና ግንባታን በማስዋብ (Façade) ስታንዳርድ ማስጠበቅና የኮሪደር ልማት ግንባታዉ ላይ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ተወያይተዋል ።
በውይይቱም የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ሃላፊ አቶ መሐመድ ኑረዲን የህንፃ እና ሌሎች ግንባታዎችን የማስዋብ (Façade) ስታንዳርድ ማስጠበቅ ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ የቀረበ ሲሆን ሰነዱም የአከባቢዉን ነዋሪዎች የከተማ ገፅታን ለመጠበቅና የአካባቢውን ደረጃ የሚያሳድግ ስታንዳርድ እና ዲዛይኖችን በመጠበቅ የግል ይዞታዎች እና የንግድ ተቋማትን ወጥ የሆነ በማድረግ እንዲሁም በአከባቢው ከደረጃ በታች የሆኑ ይዞታዎችን በመልሶ ማልማት ሂደት ውስጥ የሚለማበትን አማራጮችም ተያይዞ የቀረበ ሲሆን ህብረተሰቡም በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት አካሂዷዋል።
ህብረተሰቡም እየተሰራ በሚገኘው የኮሪደር ልማት ግንባታ ለአካባቢው የሚኖረውን ልዩ ጥቅም ታሳቢ በማድረግ እና ልማቱን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን የህንፃ እና ሌሎች ግንባታዎችን እስከ አሁን በጀመረው ልክ ከበፊቱ በበለጠ ደረጃ በመናበብ የFaçade ስራውን በአጭር ግዜ ለመጨረስ በመግባባት አስፈላጊው የባለሙያ ድጋፍ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ::
በቀጣይ ትግበራ አካባቢውን ከደረጃ በታች የሆኑትን ለማልማት እራሱ አልሚ የሚሆንበት አሰራር መዘርጋቱ መንግስት የሰጠው መመሪያ ተገቢና ህብረተሰቡን ባለቤት ያደረገ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን መልሶ ማልማቱን በአጭር ግዜ ወደ ልማት ለመግባት ወደ መግባባት ላይ ተደርሷል ::
የከተማ ገፅታን የማስዋብ ስራ ለአከባቢው ነዋሪ ብሎም ለከተማው ዕድገት የሚኖረው አስተዋፆ ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ የድርሻውን ተሳትፎ እንዲያደርግ በውይይቱ ገልፀዋል።
በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ ህብረተሰቡም ጥያቄ እና አስተያየታቸውን በማቅረብ በሰፋት የተወያዩ ሲሆን ህብረተሰቡም የቀረበውን ስታንዳርድ በትክክል በመረዳት በቀረበው ስታንደርድ መሰረት በመከወን ያለ አግባብ ከሚወጡ ወጪዎችን ከማውጣት አንዲቆጠብም ጭምር አሳስበዋል።








