በሐረር ከተማ አሚር ኑር ወረዳ በተለምዶ ገንደ ፌሮ በመባል በሚጠራው አካባቢ ለሚከናወነው የኮሪደር ልማት ከአካባቢው በልማት የተነሱ ነዋሪዎች በተገባላቸው ቃል መሰረት የሁለተኛ ጊዜ የልማት ተነሺዎች ምትክ የቤት መስሪያ ቦታ መረከባቸውን ገልፀዋል።
በተለይ የከተማ የመሬት ደረጃን የጠበቀ ቦታ በፍጥነት በመረከባቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸውም ነው የገለፁት። የኮሪደር ልማቱ ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች እና ለመኖሪያ ምቹ የሆነች ከተማን ለማስረከብ የሚያስችል ነው ያሉት የልማት ተነሺዎቹ መንግስት የጀመረውን የኮሪደር ልማት አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
በከተማ ልመትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለስልጣን ሀላፊ አቶ ጁኔድ ኑረዲን በበኩላቸው ለ 13 የልማት ተነሺዎች የከተማውን የመሬት ደረጃ የጠበቀ ቤት የመስሪያ ቦታን መፈፀሙን በመግለጽ በቀጣይም የልማት ተነሺዎቹ ደረጃውን የጠበቀና ወጪ ቆጣቢ የቤት መገንቢያ ዲዛይን እንዲያገኙ በቀጣይ አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በመጨረስ ለግንባታቸው የሚያስፈልጋቸውን የቤት ዲዛይን እንዲያገኙ የሚያደርጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ካሁን ቀደም በከተማው ለኮሪደር ልማት ተነሺዎች ምትክ የመስሪያ ቦታ መሰጠቱ የሚታወስ ነው በማለት ገልጸዋል ።






