Thursday, April 30, 2026
HomeMeetingCommunityየከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አባዲር ፕላዛ ፓርክና...

የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አባዲር ፕላዛ ፓርክና ለመንገድ ልማት ፕሮጀክት ለልማት ተነሺዎች የግንባታ ፍቃድ መስጠቱን አስታውቋዋል

በሐረሪ ክልል እየተከናወነ በሚገኘው የኮሪደር ልማት ምክንያት ለልማት ተነሽዎች በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን ምትክ ቦታ እንዲረከቡ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ስታንደርድ ዲዛይን አዘጋጅቶ ለሁሉም ተነሽዎች በምትክ ቦታቸው የከተማውን ደረጃና የአካባቢውን የመሬት አቀማመጥ እንዲሁም የህብረተሰቡን የኢኮኖሚያዊ አቅምና ማህበራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረጉ 3 የዲዛይን አማራጮች በማቅረብ በራሳቸው ምርጫ ፍላጎታቸውን ያማከለ ግንባታ የሚያኮናውኑበት ለ 26 ዜጐች የግንባታ ፍቃድ መስጠቱን አስታውቋል ።

በመሆኑም በዛሬው እለት በከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አባዲር ፕላዛ ፓርክና ለመንገድ ልማት ፕሮጀክት ለልማት ተነሺዎች የግንባታ ፍቃድ መስጠቱን አስታውቀዋል።

RELATED ARTICLES

Most Popular

Recent Comments