Thursday, April 30, 2026
HomeNews & EventCorridor Developmentየኮሪደር ልማት ስራው የሐረር ከተማን ገፅታ ለመቀየር አስችሏል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

የኮሪደር ልማት ስራው የሐረር ከተማን ገፅታ ለመቀየር አስችሏል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

የኮሪደር ልማት ስራው የሐረር ከተማን የቀድሞ ገፅታ ለመቀየር ማስቻሉን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ

በአፋር ክልል ከተማ ልማት እና ኮንስትራሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ አህመድ ኑር ሳሊም የተመራ ልዑካን ቡድን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ልዑካን ቡድኑ በክልሉ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በተመለከተ ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር መክረዋል።

በምክክሩ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በተመለከተ ለልዑካን ቡድኑ በሰጡት ገለፃ የኮሪደር ልማት ስራው የሐረር ከተማን የቀድሞ ገፅታ ለመቀየር ማስቻሉን ገልፀዋል።

ሐረር ከ 1 ሺ በላይ ዕድሜ ያስቆጠረች ዕድሜ ጠገብ ከተማ ብትሆንም ከለውጡ በፊት የከተማ ልማት ስራ ዕምብዛም ትኩረት ሳይሰጠው ከተማዋ ሳትለማ መቆየቷን ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ ከለውጡ ወዲህ ለከተማ ልማት ስራ ትኩረት በመስጠት በተሰራው የሐረር ከተማን ለኑሮና ስራ ምቹ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።

በተለይ ምቹ የተሽከርካሪ እና እግረኛ መንገዶች፤የህዝብ መናፈሻ ስፍራዎችን በመገንባት፤በከተማ ፅዳት እና ውበት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።

በከተማው የተሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለዜጎች የስራ ዕድል የተፈጠረባቸው እና የአካባቢውን ኢኮኖሚ እንዲነቃቃ ያስቻሉ ብሎም ቀድሞ የነበረውን የስራ ባህል የቀየሩ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

የልምድ ልውውጡ የአፋርና የሐረሪ ክልል ቀድሞ የነበራቸውን የእርስ በዕርስ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችል መሆኑንም አክለዋል።

ልዑካን ቡድኑ በቀጣይ በክልሉ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ይመለከታል ተብሎ ይጠበቃል።

RELATED ARTICLES

Most Popular

Recent Comments