በአፋር ክልል ከተማ ልማት እና ኮንስትራሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ አህመድ ኑር ሳሊም የተመራ ልዑካን ቡድን ሐረር ከተማ ገባ።



ልዑካን ቡድኑ ሐረር ከተማ ሲደርስ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር መዓረግ የክልሉ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አቀባበል ተደርጎለታል።
ልዑካን ቡድኑ በሐረር ከተማ በተከናወኑት የኮሪደር ልማት ስራዎች የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የመጣ ሲሆን በቀጣይ የኮሪደር ልማት ስራዎች ላይ የመስክ ምልክታ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል
