Saturday, May 2, 2026
HomeNews & EventConstructionበአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የተመራ ልዑካን ቡድኑ በሀረሪ...

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የተመራ ልዑካን ቡድኑ በሀረሪ ክልል የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን እንዲሁም የከተማ ልማት ዘርፍ ስራዎች በተመለከተ ውይይት እና የመስክ ጉብኝት አካሂዷል ።

በሀረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ል ፕሬዘዳንት ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙኽታር ሳሊህ በሀረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አቻ መካከል የሚደረገው ልምድ ልውውጥ ማድረግ ወጥነትና የተሻለ አሰራሮችን ከመዘርጋት አንፃር የጎላ ሚና እንደሚኖረው እና በልምድ ልውውጡ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችንና ስራዎችን ወደ ራስ ወስዶ በመስራት ውጤት ማምጣት የሚያስችል ነው ሲሉ ገልጸዋል ።

በውይይቱ የሀረር ማዘጋጃ ስራ አስኪያጅ አቶ ኤልያስ ዮኒስ የኮሪደር ልማት በሀረሪ ክልል የኮሪደር ልማት ትላንት ዛሬ ነገ የሚገልጽ ፅሁፍ አቅርቧል ። በከተማው እየተካሄዱ ያሉት የኮሪደር ልማት ስራዎች የስራ ባህልን የቀየሩና ለበርካታ ስራ አጥ ዜጎች ተጨማሪ የስራ እድልን የፈጠሩና እየፈጠሩ ያለው መሆኑን የኮሪደር ልማቱ አለም አቀፉን የጁገል ቅርስ ዳግም በማደስ የሐረር ከተማን ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ያደረገ ነው በማለት ገልጸዋል ።

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የተመራ ልዑካን ቡድኑም ጥያቄዎች እና አስተያየታቸውን በማንሳት ሰፊ ውይይት በማድረግ አጠናቀዋል ።

በመጨረሻም በአፋር ክልል ከተማ ልማት እና ኮንስትራሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ አህመድ ኑር ሳሊም የተመራ ልዑካን ቡድን በክልሉ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ፣ የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች እና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ስራዎችን የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

RELATED ARTICLES

Most Popular

Recent Comments