በመሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር ሂደት ፍትሃዊነት እና ግልፀኝነትን የተላበሰ እንዲሆን መልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈታ ልማታዊ የመሬት አስተዳደር እንዲኖር በርካት ስራዎች እየተሰራ ሲሆን ነገር ግን በዚህ ተግባራት ሠራተኛውም ሆነ አመራሩ ትልቅ ስራ መስራት እንደሚጠበቅበት በተለይም ባለጉዳዮች የሚስተናገዱበት ሁኔታ የመልካም አስተዳደር በተመለከተ እንዲሁም የተወሰነ የሠራተኛ ሪፎር ስራዎች ላይ ለውጦች ቢኖርም አሁን ላይ በተሻለ መልኩ ትኩረት በመስጠት አመርቂ ለውጦችን ለማምጣት በመቀናጀትና በመናበብ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ የመሬት ልማትና አስተዳደር ባለስልጣን ሃላፊ አቶ ጁነይድ ኑረዲን ገልፀዋል። በመድረኩም የ2017 የመጀመሪያ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀምና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ ለመሬት ልማትና አስተዳደር ባለስልጣን ሰራተኞች ቀርቧል ። በቀረበው ሰነድ በሰፊው እንዲወያዩበት እና በአፈፃፀሙ የታዩ ጠንካራ ስራዎችን በማስቀጠል ዝቅተኛ ስራ የታየባቸውን ለማሻሻል መስራት እነደሚጠበቅ አቅጣጫ አስቀምጧል ።የዕቅዱ መነሻ በዘርፉ ከሚስተዋሉ ተግዳሮቶች መካከል የተጎሳቆሉና የደቀቁ አካባቢዎች መኖር ፤ የመሬት ዝግጅት ስራዎች በሚፈለገው ደረጃ ለመፈጸም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር፤ የመሬት ልማትና ይዞታ አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥ በሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ የህብረተሰቡን ተሳታፊነትና ዘላቂ ተጠቃሚነት ሊያጎለብት በሚያስችል ሥራዎች ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት መሆኑን ተገልጿል ።*








