Saturday, May 2, 2026
HomeNews & EventCorridor Developmentየኮሪደር ልማት ስራው የሀረር ከተማን ለነዋሪ እና ለጎብኚዎች ምቹ እንድትሆን የሚያስችል ነው-አቶ...

የኮሪደር ልማት ስራው የሀረር ከተማን ለነዋሪ እና ለጎብኚዎች ምቹ እንድትሆን የሚያስችል ነው-አቶ ሙክታር ሳሊህ

የኮሪደር ልማት ስራው የሀረር ከተማን ለነዋሪ እና ለጎብኚዎች ምቹ እንድትሆን የሚያስችል ነው-አቶ ሙክታር ሳሊህ

ሀረር መስከረም 22/2017(ሀክመኮ):-የኮሪደር ልማት ስራው የሀረር ከተማን ለነዋሪ እና ለጎብኚዎች ምቹ እንድትሆን የሚያስችል መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር መዕረግ የሀረሪ ክልል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ ገለፁ።

በሀረሪ ክልል በሁለተኛ ዙር የሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ማስፈፀሚያ ዕቅድ ቀርቦ ውይይተ ተደርጎበታል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር መዕረግ የሀረሪ ክልል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ እንደገለፁት የኮሪደር ልማቱ ፕሮጀክቶችን አቅዶ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ የይቻላል መንፈስ እውን የሆነበት ብሎም የስራ ባህል እንዲጎለብት ያስቻለ መሆኑን ገልፀዋል።

በመጀመሪያ ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ከፍተኛ አመራሩ በጥብቅ የሥራ ዲስፕሊን በመመራት ባደረገው የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል በተሞክሮነት ሊጠቀስ የሚችል አበረታች ውጤት ተመዝግቧል።

በተለይ የኮሪደር ልማት ስራው ከተማውን ለዜጎች ምቹ መኖሪያ እና የስራ አካባቢ እንዲፈጠር ያስቻለ መሆኑን በመጠቆም ጅምር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

የሀረር ከተማ ቱሪዝም መዳረሻ እንደመሆኗ መጠን የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን ምቹ እና በቱሪስቶች ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻነት የሚያጎለብት መሆኑንም አስገንዝበዋል።

የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱ የከተማውን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት እና የትራፊክ ፍሰቱን በማሳለጥ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም አክለዋል።

በመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የተገኙ ተመክሮዎችን በመቀመር በሁለተኛው ዙር በከተማና ገጠር የሚከናወኑ ማስፋፊያዎችን በአጭር ጊዜ በጥራት እና ፍጥነት ለማጠናቀቅ
ርብርብ እንደሚደረግም ገልጸዋል።

ለስራው ውጤታማነት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ ቡድን በሁሉም ወረዳዎች የድጋፍና ክትትል ስራ እንዲያከናውን መመደቡን ገልጸዋል።

RELATED ARTICLES

Most Popular

Recent Comments