የከተማ ልማትና ኮንስተራክሽን ቢሮ ም/ል ቢሮ ሀላፊ አቶ ረኢስ ዩሱፍ ውይይቱን በመክፈቻ ንግግር አስጀምረዋል ። ኘላኑ የህብረተሰቡን ፍላጎት መነሻ በማድረግ ቤት ለቤት ከህብረተሰቡ የሚሰበሰቡ መረጃዎችን በማካተት ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን አቶ ረኢስ ዩሱፍ ገልፀዋል። በመድረኩም የወረዳ አመራሮች እና ስራው የሚመለከታቸው የከተማ ፕላን ኢኒስቲትዩት ባለሞያዎች ተገኝተዋል ።የሰፈር ልማት ፕላን (NDP) ማስጀመሪያ ፕላን የፕራይም ኮንሰልታንሲ ድርጅት በማቅረብ በቀረበው ፕለን ህብረተሰቡ የተለያዩ ጥያቄና ሀሳብ በማንሳት በሰፊው እንዲወያዩበት ተደጓል።*//*የከተማ ልማትና ኮንስተራክሽን ቢሮመስከረም 13/2017 ዓ.ም










