በ2016 ዓ.ም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሠረታዊ ፓርቲ ኮንፈረንስ የተቋሙ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ረኢስ ዩሱፍ በኮንፍረንሱ የሚታዩ ዋና ዋና ጉዳዮችን በማቅረብ አንፍረንሱን በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን የተቋሙ የመሠረታዊ ፓርቲ የ2016 ዓ.ም አፈፃፀም እና ቀጣይ የ2017 ዓ.ም ዕቅድን የመሬት ይዞታ መረጃ ና ምዝገባ ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም መሀመድ አቅርበው በስፋት ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ በተለያዪ ጊዜዎች በተቋሙ በተደረጉ ተከታታይ ውይይቶች የመሰረታዊ ድርጅት አባላት የራሳቸውን ዕቅድ ከማቀድ ጀምሮ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር መቻሉ እና በተቋሙ የመሠረታዊ ድርጅት አባላትን መረጃ አጠቃሎ የሚይዝ እንደ ተሞክሮ የሚወሰድ በተቋሙ ለምቶ የተዘጋጀ ሶፍትዌር በማበልፀግ ውጤታማ ስራ መከናወኑን በመግለጽ ተቋሙ ለፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ህንፃ ግንባታ የሞያ የፋይናንስ እና የግንባታ ግብአት አቅርቦት ድጋፍ ማድረጉ የሚበረታታ ተግባር መሆኑን አቅርበዋል።
በመጨረሻም በቀጣይ የ2017 ዓ.ም ካለፈው ድክመት በመነሳት የብልፅግና አላማን ለማስቀጠል እና የፓርቲውን እሴት የሚያጎለብቱ አባላትን በማፍራት የታዪ ክፍተቶችን ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራ ተገልፆ በኮንፈረንሱ የተገኙ አባላት በቀረበው ሰነድ ላይ አስተያየት እና ጥያቄ በማንሳት ቤቱ ምላሽ ሰቶበት በስፋት ከተወያየ በሁዋላ የ 2016 ሪፖርትን በማጽደቅ ኮንፈረንሱ ተጠናቋል።
