በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የከተማ ፕላን ኢኒስቲትዩት በፕራይም አማካሪ ድርጅት አማካኝነት በሐረር ከተማ መሰራት ላይ የሚገኙት የስድስት የሰፈር ልማት ፕላኖች(NDP) የዝግጅት አካል የሆነውን ዝክረ ሀሳብ/Draft proposal/እና የከተማ ዲዛይን /urban design / የጥናት ሰነድ ከአማካሪ ድርጅቱ በመጡ ባለሙያዎች ከተለያዩ ባለድርሻ ቢሮዎችና ተቋማት ለተዋቀረው ቴክኒካል ኮሚቴ አቅርበዋል።
በቀረበው ሰነድ ላይም ሰፊ ማብራሪያ ተሰቷል።
ከቴክኒካል ኮሚቴው አባለት በጥናቱ ላይ ጠቃሚ አስተያየቶች እና መጨመር ነጥቦችን አንስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎበት ለቀጣይ ስራዎች አቅጣጫ ተሰቷል።













