Thursday, April 30, 2026
HomeNews & EventConstructionየከተማ ልማትና ኮንስተራክሽን ቢሮ የክልሉ አስፈፃሚ አካላት ያደረጉትን የክልል የ9 ወር እቅድ...

የከተማ ልማትና ኮንስተራክሽን ቢሮ የክልሉ አስፈፃሚ አካላት ያደረጉትን የክልል የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ የተነሱ ሀሳቦች እና የትኩረት አቅጣጫዎችን ከማኔጅመንት አባላት ጋር ውይይት አካሄደ።

የከተማ ልማትና ኮንስተራክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙኽታር ሳሊህ የተቋሙ የ2017 የ9 ወር እቅድ አፈጻጸም ከማኔጅመንት አባላት ጋር ላለፉት ሁለት ቀናት በክልሉ አስፈፃሚ ተቋማት፤የክልሉ ሴክተር መ/ቤቶች እና ወረዳዎች ባደረጉት የግምገማ መድረክ የተነሱ ሀሳቦች እና በክቡር ፕሬዝዳንት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል ።በውይይቱ በዋናነት የአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ተግባራት በማዘመንና በማሳለጥ የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖር ፤ ገቢን ከማሳደግ አንፃር በትኩረትና በትጋት እንዲሰራ እንዲሁም በዚህ 9 ወር ሳይሰሩ የቆዩ እና የተንጠባጠቡ ስራዎችን ለይቶ በቀሪ ግዜ ውስጥ እቅድ ሪቫይዝ በማረግ መፈጸም እንደሚገባ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ከወዲሁ የ 2017 ማጠቃለያ እና የ2018 በጀት አመት የዝግጅት ምዕራፍ ዝግጅት እንዲደረግ በማለት የከተማ ልማትና ኮንስተራክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙኽታር ሳሊህ አሳስበዋል ።በመጨረሻም ስራዎች በቀጣይ በቀሪ 3 ወራት በርብርብ በጥራትና በፍጥነት እንዲሰሩ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል ፡፡

RELATED ARTICLES

Most Popular

Recent Comments