በስልጠናው በ Emotional Moral Intelligent and Mind Set)ን በተመለከተ ሁለት ሰነድ ቀርቦ በስፋት ውይይት ተካሂዷል ።
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የከተማ ፕላን ኢኒስቲቲዩት ሀላፊ አቶ ማእሩፍ አብዲ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ስልጠናውን ያስጀመሩ ሲሆን ስልጠናውም ትክክለኛ አመለካከት እና ስብእናን ትኩረት ያደረገ እና ለተቋሙ ትክክለኛ አመለካከት ያለው ሲቪል ሰርቫንት ለመፍጠር የሚያስችል አስፈላጊ እና ወሳኝ ስልጠና መሆኑንና ቀጠይነት ያለው መሆኑን አቶ ማእሩፍ አብዲ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልጿል። አክለውም የሠራተኛ ሥነ-ምግባር በእያንዳንዱ ተቋም ወይም ማህበረሰብ ውስጥ ስህተት የሆኑት ድርጊቶች ወይም ተግባሮች እንዳይፈጸሙ፣ ብልሹ አሰራር እንዴት መቅረፍ እንደሚቻል እንዲሁም ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ እና አጠቃላይ የአስተሳሰብ፣ የአመለካከት እና የተግባር አፈጻጸሞች የሚመሩበት ሥርዓት እንዲዘረጋ የሚያደርግ በመሆኑ ስልጠናውን አስጀምረዋል ።በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በ(emotional Moral Intelligent and Mind Set)ዙሪያ ለቢሮው ሠራተኞች ስልጠና ተሰጥቷል ።
RELATED ARTICLES
